የቂያም ቀን 3 ስራዎች ከትልቅነታቸው የተነሳ ሚዛን ላይ

አይገቡም …
1)ለሰዎች ይቅርታን ማድረግ ( ﺍﻟﻌﻔﻮ ﻋﻦ ﺍﻟﻨﺎﺱ )
* ምንዳቸው ምን ያህል እንደሆነ ወሰን አልተሰጠውም..
አላህ ﷻ እንዲህ ይላል …
ﻓَﻤَﻦْ ﻋَﻔَﺎ ﻭَﺃَﺻْﻠَﺢَ ﻓَﺄَﺟْﺮُﻩُ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ
” ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው … ”
2) ሰብር ( ﺍﻟﺼﺒﺮ )
* ምንዳቸው ምን ያህል እንደሆነ ወሰን አልተሰጠውም..
አላህ ﷻ እንዲህ ይላል …
ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﻳُﻮَﻓَّﻰ ﺍﻟﺼَّﺎﺑِﺮُﻭﻥَ ﺃَﺟْﺮَﻫُﻢ ﺑِﻐَﻴْﺮِ ﺣِﺴَﺎﺏٍ
” ታጋሾች ምንዳቸውን የሚሰጡት ያለግምት ነው።”
3) ፆም ( ﺍﻟﺼﻴﺎﻡ )
ረሱል ﷺ አሉ
አላህ ﷻ እንዲህ አለ:-
ﻛﻞ ﻋﻤﻞ ﺍﺑﻦ ﺁﺩﻡ ﻟﻪ ﺇﻻ ﺍﻟﺼﻮﻡ ﻓﺈﻧﻪ ﻟﻲ ﻭﺃﻧﺎ ﺃﺟﺰﻱ ﺑﻪ .
“ሁሉም የአደም ልጅ ስራ የርሱ ነው
ከፆም በስተቀር ፆም የኔ ነው እኔም ነኝ ምንዳውን
የምመነዳው።”
{ ቡኻሪና ሙስሊም }
* ምንዳቸው ምን ያህል እንደሆነ ወሰን አልተሰጠውም..
የቂያም ቀን ተጣሪው የታሉ ምንዳቸው በአላህ ላይ የሆነው
ሲል ይጣራል …
* ፆመኞች
*ታገሾችና
*ይቅር ባዮችን ብቻ ይቀበላቸዋል።
እኔንም እናንተንም በዚህች ጥሪ ከሚጠሩት አላህ ያርገን!!

Leave a comment